Construction Machinery / Construction Machinery and Equipment / Machinery and Equipment / Others

በደ/ብ/ሕ/ክ/መ በጋሞ ዞን በቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2013 ዓ.ም በመደበኛ በጀት የተለያዩ ለመንገድ ሥራ አገልግሎት የሚውል ማሽነሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ብ/ሕ/ክ/መ በጋሞ ዞን በቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2013 ዓ.ም በመደበኛ በጀት የተለያዩ ለመንገድ ሥራ አገልግሎት የሚውል ማሽነሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል ::

ስስሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ በመንግስት ግዥ አዋጅና ደንብ መመሪያ መሠረት

 1.  የታደስ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣
 2. የዘመኑ ግብር የተከፈለበት መረጃ ማቅረብ የሚችል ፣
 3. የግብር ከፋይነት ምዝገባ ቁጥር /Tin Number/ ያላቸው ፣
 4. ቫት ተመዝጋቢ የሆነ መረጃ ማያያዝ ይኖርባቸዋል ፣
 5. ከሽያጭ ዋጋ ላይ የመንግስት ግብር 2% ለመክፈል ፈቃደኛ የሆኑ ፣
 6. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ፣
 7. የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
 8. የጨረታው ሁኔታ በአይተም/በጥቅልል ሊሆን ይችላል ፣
 9. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በመለየት ኦርጅናሉን በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማስገባት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ በቁጫ አልፋ ወ/ፋጽ/ቤት ቢሮ ቁ 3 ላይ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ ::
 10. . በጨረታው ሂደት ላይ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለበት፡፡
 11. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 | አስራ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል።
 12. ተጫራቾች የዕቃዎችን ዝርዝር የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቁጫ አልፋ ወፋጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት የሚችሉ ይሆናሉ ::
 13. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ 10,000.00/አስር ሽህ ብር/ብቻ ከጠቅላላ ዋጋ በባንክ የተረጋገጠ CPO በጥሬ በቼክ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 14.  የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው የጨረታው ማብቂያ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይሆናል፣
 15. ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል ፣
 16. በጨረታው አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ዕቃውን እስከ ቁጫ አልፋ ወ/ፋ/ጽ/ቤት ድረስ የጫኚ የአውራጅና የጭነት ወጪን በመሸፈን ማቅረብ ይኖርባቸዋል ::
 17. ተጫራቾች ወይም የተጫራቹ ወኪል_ ያለመገኘት ጨረታውን መክፈት አያስተጓጉልም፡፡
 18. . 16ኛው ቀን ሰንበት ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል ::

ማሳሰቢያ ፦ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0916876946/0916108292/098466 6189 ደውሎ ይጠይቁ፡፡

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ በጋሞ ዞን

በቁጫ አልፋ ወረዳ የፋይናንስ ጽ/ቤት