ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደብ/ብ/ሕ/ክ/መ የኮንሶ ዞን ካራት ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት ለሴክተር መ ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- የጽ/መሣሪያ፣
- የኤሌክትሮኒክስ፣
- የፈርኒቸር እና
- ሞተር ሳይክል ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና በዘርፉ የንግድ ምስክር ወረቀት ያላቸው
- በዘርፉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN Number/ ያላቸው
- በዘርፉ የተጨማሪ እሴት ታክሰ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑ
- በዘርፉ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው
- በዘርፉ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ያላቸው
- ተጫራች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ለጽ/መሣሪያ 100 /አንድ መቶ ብር ለኤሌከትሮኒከስ 100 /አንድ መቶ ብር/፣ለፈርኒቸር 50 /ሃምሳ/ ብር እና በሞተር ሣይከል 50 /ሃምሳ ብር/ ብቻ ለኮንሶ ዞን ካከ/አስ/ር ገ/ባ/ቅ/ጽ/ቤት ገቢ አሰባሰብ ዋና የሥራ ሂደት ከፍለው ደረሰኝ በመያዝ በኮንሶ ዞን ካ/ከ አስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ር ዋና ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ በአራቱም ዘርፍ ማለትም ለጽ/መሣሪያ 6,000 /ስድስት ሺህ/ ብር፣ ለኤሌክትሮኒክስ 10,000 /አሥር ሺህ/ ብር፣ ለፈርኒቸር 3,000 /አሥር ሺህ/ ብር እና ሞተር ሳይክል 10,000 /አሥር ሺህ/ ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ/CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከቴክኒካል ኦርጂናል ዶክሜንት ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቶች ጨረታው በአንድ ኤንቨሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ለእያንዳንዱ ዘርፍ የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ ፋይናንሻል ኦርጅናል 1 ፋይናንሻል ኮፒ) እንዲሁም ቴክኒካል ኦርጅናል 1 ቴክኒካል ኮፒ ለየብቻ ለይቶ በእራት ፖስታ በማድረግ በአንድ በታሸገ እናት ፖስታ ውስጥ አድርገው በላዩ ላይ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፤ አድራሻ፤ስምና ፊርማ በማሳረፍ በ6ኛው የስራ ቀን ካ/ከ/አስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው በ16ተኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሲሆን የሚከፈተው በዚሁ ዕለት ልክ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾችወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ጨረታው ይከፈታል በተባለበት በ16ኛው ቀን በመንግስት የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ይከፈታል።
- አሸናፊው ድርጅት ላሸነፉት ዕቃ የውል ማስከበሪያ ዋስትና 10% ይዘው ቀርቦ ውል ባይገባ በዘርፉ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ውርስ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
- ተጫራቾች ተሟልተው ያለመገኘት የጨረታው አከፋፈት ሥነሥርዓት ሊያስተጓጉል አይችልም።
- በጨረታ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልጾ የሚሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ዕቃዎቹን በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዘው ለመ/ቤታችን ማስረከብ ይኖርበታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
- ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር- 0923368085/0916161133 ላይ ደውለው ያግኙን
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ የኮንሶ ዞን
የካራት ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
ካራት