የሊዝ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጐንደር ዞን የጉና በጌምድር ወረዳ የክ/ድንጋይ ከተማ መሪ ማ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ለማስተላለፍ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 እና በሊዝ መመሪያ ቁጥር 1/2005 መሰረት በ2012 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ አገልግሎት 11 ለድርጅቱ 2 ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
- መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 በመክፈል ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 10 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡30 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በ4፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በክ/ድንጋይ ከተማ መሪ ማ/ቤት አዳራሽ ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ መለጠፊያ ሰሌዳ ወይም በስልክ ቁጥር 058 2510224/0230 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ቦታውን በመስክ ለመጎብኘት ከፈለጉ ከማ/ቤቱ ድረስ በመምጣት ከጨረታ ኮሚቴው ጋር መጎብኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለድርጅት 15 በመቶ ለመኖሪያ 10 በመቶ ህጋዊ በሆነ ባንክ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማስታወቂያው በጋዜጣ ከላይ በተጠቀሱት መስፈርቶች መሰረት በጋዜጣ እንዲወጣልን እንገልፃለን፡፡
የጌምድር ወረዳ የክ/ድንጋይ ከተማ መሪ ማ/ቤት