ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጐንደር ዞን የአንዳቤት ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2013 ዓ/ም በጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚውል
- ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ፣
- ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለበት፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ ቲን ያላቸው፣
- የግዥ መጠኑ 50 ሺህ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለመሣተፍ ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚቻሉ መሆን አለበት፡፡
- . የሚገዙ ዕቃዎች ዓይነት ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 በመክፈል ግ/ፋ/ን/አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 25 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ በሚወዳደሩበት ብር የዕቃው ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወጥ በታሸገ ፖስታ በአ/የመ/ደ/ሆ/በግ/ፋ/ን/ አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 25 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- . ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 25 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ ቀን 3፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከ14/03/2013 ዓ/ም እስከ 28/03/2013 ዓ/ም
- . መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃዎች ከመ/ቤቱ ማድረስ አለበት፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ውል ለመያዝ ሲመጡ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- . ከጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ፖስታው ላይ እና ሰነዱ ላይ ማህተም መረገጥ አለበት፡፡
- ጨረታውን የሚከፈትበት የበአል ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን ይከፈታል፡፡
- . ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ዋጋ ነው፡፡
- በጨረታው ማሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0924537435 እና 0921288015 መደወል ይችላል፡፡
የአንዳ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል