ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጎንደር ገ/ኢ/ል/መምሪያ የታ/ጋ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በስሩ አገልግሎት ለሚሰጣቸው በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል በመደበኛ በጀት
- የተዘጋጁ ልብሶች
- 2ኛ የተለያዩ ጫማዎች
- 3ኛ ብትን ጨርቅ ግዥ እንዲፈፀምላቸው በጠየቁት መሠረት
ከተጫራቾች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስቀረብ ይፈልጋል:: ስለዚህ ተጫራቾች፡-
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው፣
- የሞሉት ዋጋ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/የቫት/ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የአቅርቦት ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሸን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የአቅርቦት ዓይነት 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው:: ይህም ገንዘብ አሸናፊ ከሆኑ ከውል ማስከበሪያ ጋር ተጨምሮ የሚታሰብ ይሆናል:: ተሸናፊ ከሆኑ ደግሞ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣብ በአንድ ወጥ በሆኑ ፖስታዎች የድርጅቱን ክብ ማህተም በመምታትና በጥንቃቄ በማሸግ ታ/ጋ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሰራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለ ጀምሮ በሚቆይ የአቅርቦት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡00 ላይ ይዘጋል:: በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል:: ሆኖም ግን ተጫራቾች በራሣቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙም የጨረታውን መክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለሚተላለፍ ውሣኔዎች ተገዥ ይሆናሉ::
- . መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- አሸናፊው የሚለየው በጠቅላላ ድምር ውጤት/በሎት/ በመሆኑ የተጠየቁትን ዝርዝር አካተው መሙላት አለባቸው::
- . መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- . በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ታ/ጋ/ወ/ግ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 2680218 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::
የታች ጋይንት ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት