ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጎንደር ዞን የአንዳቤት ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
- ሎት 1. የጽህፈት መሣሪያ፣
- ሎት 2. የፈርኒቸር ዕቃዎች፣
- ሎት 3. የህትመት ግዥ፣
- ሎት 4. የተዘጋጁ ደንብ ልብስ፣
- ሎት 5. የተዘጋጁ ጫማዎች፣
- ሎት 6. የደንብ ልብስ ብትን ጨርቆች፣
- ሎት 7. የደንብ ልብስ ስፌት፣
- ሎት 8. ኤሌክትሪክ/ የመብራት/ ዕቃዎች፣
- ሎት 9. የጠመኔ /ቾክ/ ግዥ፣
- ሎት 10. የኤሌክትሮኒክስ ግዥ፣
- ሎት 11. የውሃ ዕቃ፣
- ሎት 12. የግንባታ ዕቃዎች እና
- ሎት 13. የስሚንቶ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት
ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የተጋበዛችሁ በሙሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይጠብቅባችኋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/ቲን ናምበር/ ያላቸው፣
- የግዥ መጠኑ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን ጠቅላላ የመወዳደሪያ ዋጋ ለእያንዳንዱ ሎት 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ /ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በማድረግ/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማስያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 50 ብር መግዛት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአንዳቤት ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር ግዥ ቢሮ ይከፈታል፡
- የጨረታው መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ማሻሻያ ማድረግና ራሳቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከተገለፁበት ቀን ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ክፍል ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ /ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በማድረግ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ውል መውሰድ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ ከጨረታው 20 በመቶ የመቀነስና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ሲሆን ሁሉም የዕቃዎች ዋጋ መሞላት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ስማቸውን፣ ፊርማቸውና ሙሉ አድራሻቸውን መግለጽና የድርጅቱን ማህተም መርገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- . ለበለጠ መረጃ በአካል ቢሮ ቁጥር 3 በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 547 06 8 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
አንዳቤት ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት