የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የፋርጣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 2. የቢሮ መገልገያ፣
- ሎት 3. የጽዳት እቃ፣
- ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- ሎት 5. የደንብ ልብስና ፣
- ሎት 6. የስፖርት ትጥቅ ፣ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ማሟላት ያላቸው፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የሚሞላዋ ዋጋ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የመጫረቻ ሰነዶችን ይህ ግልጽ ጨረታ በአየር ላይ ከዊለበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ በፋርጣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በመምጣት ከዋናው ጋር ሊገናዘብ የሚችል ፎቶ ኮፒ ማስረጃ በማቅረብ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 30 ብር በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ለ/ጽ/መሳሪያ ብር 5000.00፣ ለደንብ ልብስ ብር 5000.00፣ ለሌሎች ለእያንዳንዳቸው ብር 1000.00 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /በጥሬ ገንዘብ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በባንክ ያስያዙትን ገንዘብ /ስፒኦ/ ወይም /ጥሬ ገንዘብ/ ከመ/ቤታችን ገቢ ያደረጉበትን የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ አሽገው ፋ/ወ/ገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ ቤት ብለው በዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ቢሮ ቁጥር 7 እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ድረስ ማስገባት ሲቻል የሚታሸገውም በዚሁ ሰዓት ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ሲቻል በዚሁ ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት /ባይገኙም/ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መከፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው የሚለየው በጥቅል /በሎት/ አሳናፊ ይሆናል፡፡
- የሚገዙ እቃዎች አቅርቦቱ ደቡብ ጎንደር ዞን ደ/ታቦር ከተማ ፋርጣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስቶር ክፍል ሲሆን የእቃዎች ርክክብ የሚፈጸመው በሙያተኛ ተረጋግጦ ነው፡፡
- የሚገዙትን እቃዎች ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 441 30 36 ደውለው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የፋርጣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት