የሊዝ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8/1 መሰረት በ2013 በጀት አመት ለ1ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ ቤት ብዛት 12፤ለድርጅት ብዛት 33 እና ለማህበራዊ ተቋም 1 በድምሩ 46 ቦታዎችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል ፡፡በመሆኑም ፡-
- መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 250 /ሁለት መቶ ሃምሳ/ ብር ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጧቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 11፡30 ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በቢሮ ቁጥር 3 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡30 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በ3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ካልሆነም ተወካዮችም ሆነ ግለሰቦቹ ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በነ/መ/ከ/አስተዳደር ቀበሌ 03 ከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
- . ይህ ማስታወቂያ ተግባራዊ የሚሆነው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይየስራ ቀናት ይሆናል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጀ ከፈለጉ በጽ/ቤቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ወይም በስልክ ቁጥር 0584450192፤ 0584451366፤ 0584451182 ወይም 0584451360 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ሌሎች ተጨማሪ ዝርዝር ሃሳቦችን /ህጎችን/ከሚሸጠው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ ጩረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የነፋስ መውጫ ከ/አስ/ከ/ል/ቤ/ኮን/አገልግሎት ጽ/ቤት