ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ወሎ ዞን በተንታ ወረዳ የአጅባር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2013 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉትን
- የደንብ ልብስ፤
- የጽህፈት መሳሪያ፤
- ኤሌክትሮኒክስና፣
- የኤሌክትሪክሲቲ እቃዎች፣
- የግብርና እቃዎችና
- የህንጻ መሳሪያዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡
- ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነምበር/ ያላቸው ለመሆኑ ማረጋገጫ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግዥ መጠን ብር 50,000 /ሀምሳ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃወች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የሚገዙት እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን / ከጫረታ ሰነድ ማገኘት ይቻላል
- ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 20 ብር በመክፈል ከአጅ/ፖሊ/ቴክ/ኮሌጅ ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/ስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር1 ማገኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቶች የጫረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃዎን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፈያ ትእዛዝ ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለበት፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመ/ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ ገቢ ተደርጎ ካርኒው ከሰነዱ ጋር አብሮ ከሳጥኑ ውስጥ መግባት አለበት ፡፡ ደረቅ ቸክ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- የጫረታዉ አሸናፊ መሆን የሚችለዉ በተጫረቱበት ዘርፍ በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ ዋጋ የሞሉ መሆኑ ታዉቆ በሰነዱ ጥቅል እቃወች ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀ ቀን በኋላ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ከጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘን ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ መሲያዝ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ መኪሎቻቸዉ በተገኙበት በአጅባር ፖሊ/ቴክ/ኮሌጅ ዉስጥ የጨረታ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን ከጧዋቱ 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ስአት በይፋ ይከፈታል፡፡ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አጅ/ፖሊ/ቴክ/ኮሌጅ ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/ስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገት ይቻላል፡፡
- አሸናፊው ተጫታች ያሸነፈውን እቃ መ/ቤቱ ከሚፈለግበት ቦታ ድረስ በራሱ ወጭ ማቅረብ አለበት፡፡ በተጨማሪም የሚቀርቡ እቃዎችን በባለሙያ እየተረጋገጠ የምንረከብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድዱ ማገኘት ይቻላል፡፡ እንድሁም የሚጠየቁትን ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ መሞላት አለበት፡፡ ሆኖም ስርዝ ድልዝ ካለው ስለመስተካከሉ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ በጨረታው በቀረቡ እቃዎች መጠን 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
- በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ግዥ ክፍል ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 441 04 70 በመደወል ማገኘት ይቻላል፡፡
- በዚህ ጨረታ ያልተገለጸ ጉዳዮች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
የአጅባር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ