ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ወሎ አስተዳደር ዞን የተንታ ወረዳ ፍ/ቤት የ2013 በጀት አመት ለቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ እቃዎችን
- ሎት 1 የደንብ ልብስ ፣
- ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 3 የጽዳት እቃዎች፣
- ሎት 4 ልዩ ልዩ ህትመት ፣
- ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት 6፣ ፈርኒቸር ወይም /ቋሚ/ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታማሉ ተጫራቾች በጨረታዉ መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- ከላይ በተጠቀሱት የአቅርቦት ዘርፎች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የግብር ክፍያ መለያ ወይም /ቲን/ ያላችሁን ማስረጃዎቹን ማቅረብ የምትችሉ፡፡
- የግዥ መጠን ብር 50 ሽህ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነትን የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ከተንታ ወረዳ ፍ/ቤት ከእለት ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ ቁጥር 5 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሎት የማይመለስ ብር 10/አስር ብር/ ከፍለዉ ከተንታ ወረዳ ፍ/ቤት ከእለት ገንዘብ ተቀባይ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ / ለሚወዳደሩበት እቃ የሚሞሉትን ጠቅላላ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ዋጋ የባንክ ትዛዝ ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ወይም የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በስማቸው የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች ያሸነፈዉን ዋጋ በተናጠልም ሆነ በጥቅል ዋጋ ከ 10.000 /አስር ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ ሁለት በመቶ የሚከፍል መሆኑን አይዘንጉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተንታ ወረዳ ፍ/ቤት ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በተንታ ወረዳ ፍ/ቤት ዉስጥ ጨረታዉ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 16ኛዉ ቀን ላይ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ መሆን የሚቻለዉ የተጫረቱበት ዘርፍ በሎት ዝቅተኛ ዋጋ የሰጡ መሆኑን ታዉቆ ለሞሉት ጥቅል እቃዎች ዋጋ ማሲያዝ አለበት፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉትን አቅርቦት ከተንታ ወረዳ ፍ/ቤት ን/ክፍል ድረስ በራሳቸዉ ወጭ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊዉ በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለ 5 ተከታታይ የስራ ቀን ዉል መፈጸምና የዉሉን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ ማስያዝ አለበት፡፡
- ሌሎች ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሁነዉ የእቃዉን ብዛት እስከ 20 በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን የበአል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለዉ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰአት ይሆናል
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- አቅራቢዉ በዉሉ መሰረት በጊዜዉ አጠናቆ ባያቀርብ በዉሉ የተመለከተዉን ገንዘብ መጠን ላይ በየቀኑ 0.01 በመቶ ወይም 1መቶኛ መቀጫ እንደሚከፍል ማወቅ አለበት፡፡
- ተጫራቾች አንዱ በአንዱ ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይቻልም፡፡
- በጨረታዉ መሳተፍ የምትፈልጉ ስለጨረታዉ ዝርዝር መግለጫ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0334410261/0334410029 ወይም 0938434845 በመደወል ማገኘት ይችላሉ፡፡
የተንታ ወረዳ ፍ/ቤት