የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2012
በደቡብ ክልል የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ባለው በጀት ለኮርት ኬዝ ሥራ የሚውሉ ማሽነሪ ዕቃዎችን
- Finger print attendance machine
- CCTV material & network equipment በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ፦
- ተጫራቾች የ2012 ዓም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉና የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የሚያቀርቡት ብር 3, 000 /ሦስት ሺህ ብር/ በተረጋገጠ ባንክ በሲፒኦ /CPO/ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል በመንግሥት የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ቀርበው ከፍ/ቤቱ ግፋን ደጋፊ የሥራ ሂደት ክፍል የጨረታውን ሰነድ መግዛት የሚችሉ፣
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ግፋን ደጋፊ የሥራ ሂደት ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ በዚሁ ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፣
- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀናት ከመደበኛ የሥራ ቀናት ውጪ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን እንደ ጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን ይቆጠራል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ቫትን/ የሚያካትትና የማያካትት መሆኑን መግለፅ አለባቸው፣
- የጨረታ አሸናፊው እቃውን እስከ ፍ/ቤታችን ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት ፣
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የቀረበው የጨረታ ሰነድ መጠየቅ ማሻሻል ወይም ከጨረታው እራሱን ማግለል አይችልም፡፡
- ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳስቢያ፡-
አሸናፊው ተጫራች እቃውን በተሰጠው ጊዜ ገደብ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
አድራሻ፡በደቡብ ብ/ብ/ህ/ከ/መንግሥት
ጌዲኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ዲላ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ -046-331-3425
046-331-2657 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት