በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ክልል እርሻና ተፈ/ሀ//ቢሮ የወላይታ ሶዶ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ ኮሌጅ በ2012 በጀት ዓመት ከተያዘው በጀት ለመማር ማስተማር ሥራ የሚውሉ የተለያዩ መሣሪያዎችን ማለትም
- ደንብ ልብስ፣ የፕሪንተር ቀለም፣ የተሽከርካሪ ጎማ፣ የተማሪዎች መመረቂያ መጽሔት፣
- የህንፃ መሣሪያ፣ የጽዳት ዕቃ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣
- የትምህርት መሣሪያ እና ተማሪዎች መመረቂያ ባይንደርን ጨምሮ በ2ኛ ዙር ድጋሚ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ስመሳተፍ ያሚችሉ፣
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን የግብር ግዴታቸውን የተወጡ፣
- የተእታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የቲን ሠርተፊኬት ያለው፣
- የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፣
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ/ ዶክመንት/የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ስም ተከፍቶ በሚገኘው አካውንት ቁጥር 1000018208443 በማስገባት የባንክ አድቫይስ በመያዝ ከወላይታ ሶዶ ግዛቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ግዥ ክፍያ ንብረት አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሠነድ ኦሪጅናሉን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውንና የድርጅቱን ስም በመጥቀስ ግብርና ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 41 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ከ15ኛው ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ሰዓት በኮሌጁግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 41 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበትን ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠለት ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝና የማይነበብ ነገር ሊኖር አይገባም፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች እስከ ኮሌጃችን ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
መረጃ ስልክ ቁጥር፡ 0465513984 ማነጋገር ይቻላል፡:
የወላይታ ሶዶ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ