የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን የምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
እነዚህም፡
- የግንባታ ቁሳቁሶች
- የቧንቧ ዕቃዎች
- የተለያዩ አላቂ የቢሮ እና የጽህፈት መሣሪያዎች
- የማዕድን ምርት ግዥ ከነማጓጓዣ
ስለሆነም በዚሁ መሠረት፡
- በዘርፉ የንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቲን ነምበር ያለው፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ፣
- የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፣
- የመኪና ኪራይ የጫኝ እና አውራጅ በአሸናፊ ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ንብረቶችን እስከ ምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለማድረስ ፈቃደኛ የሆነ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የማዕድን ምርት ግዥ ከነማጓጓዣ ብር 5000፤ የግንባታ ቁሳቁሶች ብር 5000፤ የቧንቧ ዕቃዎች ብር 5000፤ የተለያዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የጽህፈት መሣሪያዎች ብር 5000 CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በወረዳውገቢዎች ባለሥልጣንቅ/ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 50 በመክፈል እና ደረሰኙን በመያዝ የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ ከወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናሉንና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በመጨመር ሙሉ አድራሻውን በመግለጽ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እንዲጨምሩ እያሳሰብን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ልክ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የጨረታ ሰነድ በተከፈተ በሰባተኛው ቀን የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል ይፈራረማል፡፡
- የጨረታው ሣጥን ምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 ይገኛል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 0464520015 /0464520009
በጋሞ ዞን ምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ብርብር