በድጋሚ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/በወላይታ ዞን ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2012 ዓ.ም ከህብረተሰብ ተሳትፎ በተሰበሰበው በጀት በዳሞት ፑላሳ ወረዳ ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት አማካይኝነት በወረዳ ውስጥ ላሉት ሚሊሻ(የአካባቢ ጥበቃ መከላከያ) ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ የንግድ የሥራ ድርጅቶች
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል ፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የቲን ተመዝጋቢ የሆነ፤
- የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 16 መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ዕቃውን እስከ አጫራች መስሪያ ቤት ድረስ አምጥቶ ለማስረከብ ፍቃደኛ የሆነ፤
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና የኦርጅናሉ አንድ(1) ፎቶ ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውንና የድርጅቱን ስም በመጥቀስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል ፤
- የጨረታ ማስከበርያ ብር 15000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በማንኛውም ባንክ የተመሰከረለት CPO በኦርጅናል ሠነድ ውስጥ ታሽጎ ማቅረብ የሚችል ፡፡
- በጨረታው አሸናፊ ከሆኑ ውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችል፣
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አሥራ አምስት) በተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው በ16ኛው የሥራ ቀን 2/10/2012 በ4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 በዳ/ፑ/ወፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 16 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት በነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበቡና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም፡፡
ማሳሰቢያ፡– መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ እና ቢድ ቦንድ የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 0468932510 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ ::
በወላይታ ዞን ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት