የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2013 ዓም የበጀት ዘመን ሊያሰራ ላቀደው የከፍተኛ ፍ/ቤት አጥር እና የግቢ መግቢያ በር ስራ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡በኮንስትራክሽን ዘርፍ ፍቃድ ያላቸው ደረጃ 6/GC-6/ BC-6/ እና ከዚያ በላይ፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት በሚመጡት ጊዜ ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግሉ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ፣ የንግድ ፍቃድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ምስክር ወረቀት ኦርጅናሉን ይዞ በመቅረብ በቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የግዥ ፋይ/ንብ/አስተዳደር የቢሮ ቁጥር 9 የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 300 ብር በመከፈል ሙግዛት ይጠበቅባችኋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ለበጀት ዓመቱ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ፣ የንግድ ፍቃድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ፣የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ የምስክር ወረቀት በተገቢው ሁኔታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 60,000 /ስልሳ ሺህ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
- 5. ተጫራቾች የገዙት ሰነድ /ፋይናንሻል እና ቴክኒካል/ ከላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እያንዳንዱ ለየብቻ በሰም በታሸገ እና በጥቅል በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- እያንዳንዱ ፖስታ በሰም ታሽጎ ማህተም በመምታት፣ ሙሉ አድራሻ በመፃፍ እና በመፈረም ኦርጅናል ኮፒ የሚል ፅሁፍ መፃፍ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ የተጫራቾች ህጋዊ ወኪል ፊርማ እና እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
- እያንዳንዱ ፖስታ የሚወዳደሩበትን የስራ ቦታ፣ የተቋራጩ አድራሻና የተወካዩን ስልክ ቁጥር በሙግለፅ መፃፍ አለበት፡፡
- ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚታሸገው ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ተኛው ቀን በቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የግዥ ፋይ/ንብ አስተዳደር የቢሮ ቁጥር 9 ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ስማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ተኛው ቀን በቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የግዥ ፋይ/ንብ/ አስተዳደር የቢሮ ቁጥር 9 ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ፦ በስልክ ቁጥር 0473351027/0473351278/0473350090
የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
ሚዛን አማን