የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት በጎፋ ዞን ሣውላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2013 ዓ.ም የስልጠና ወርክ ሾፕ ግንባታ ለማስገንባት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑንም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች፡
- GC/BC – እና ከዚያ በላይ የሆኑ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና በ2013 ዓ/ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ ተእታ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ከሚመለከተው ክፍል የተሰጠ ታክስ ክሊራንስ ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ ::
- ተጫራቾች የአንድ ዓመት ታክስ ክሊራንስ/ TAX CLEARANCE /ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች ከአሰሪ መ/ቤት የተሰጠ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ቢያንስ ሁለት ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ ሆነው የመልካም ስራ አፈጻጸም የመጨረሻ ዙር ክፍያ ሰርቴፍከት የጊዜያዊ ርክብክብ ቨርቫልና የሥራው ልክ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዶክመንቱ የማይመለስ ብር 300.00 / ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከሣውላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፤ በግዥ ን/አስ/ር ደ/ሥ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 21 በመቅረብ የንግድ ፈቃዳቸውን ኮፒ በመያዝ መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ከጨረታው ሠነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ እና ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናሉን በአንድ ላይ በማሸግና 2 የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቅስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ21 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ሳውላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥ ን/አስ/ር ደ/ሥ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 21 ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም።
- ተጫራቾች በጨረታ መክፈቻ ንባብና በሂሳብ ማስተካከያ ልዩነት 2% በላይና በታች መሆን የለበትም።
- ተጫራቾች አንድ ሰነድ ብቻ በመግዛት መወዳደር ይችላል፡፡
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ሲያገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስ.ቁጥር 0467771707 ፣ 0467770614 ፤0467771498 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።
በደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት በጎፋ ዞን ሣውላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ