ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት በካፋ ዞን የጊምቦ ወረዳ ሴቶች ሕፃ/ወጣ/ጉ/ጽ/ቤት በ2012 የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ የተገነባውን የወጣቶች መዝናኛ ማዕከል ዙሪያውን በLTZ ብረት እና በጋቦን ሽቦ አጥር ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት፡
በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ያሳደሱ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው እንዲሁም በመንግሥት ግዥ እንዲሳተፉ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
- BC/GC ሆኖ ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ የሆነ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል::
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሠነድ ከጊምቦ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 ቀርቦ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::
- ጨረታው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን ታሽጎ በዕለቱ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: ባይገኙም የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
- ተጫራቾች ስገዙት የጨረታ ሠነድ በሚጠይቀው መሠረት ሙሉ ዶክመንት በማሟላት ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት ለየብቻው በፖስታ በማሸግ ከሁለት ኮፒ ጋር በእናት ፖስታ በማሸግ በ22ኛው ቀን ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ካሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋላይ የውል ማስከበሪያ 10% የማስያዝ ግዴታ አለበት፡፡
- ጨረታው የሚታሸግበት ቀን ቅዳሜ/እሁድ ወይም ከሥራ ቀን ውጪ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሽግ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0472220490/055 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጊምቦ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት