የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2013
በደቡብ ብብ/ሕ/ክ/መ/በውሃ ማዕድንና ኢነርጅ ልማት ቢሮ በመደበኛና በሌሎች በጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የሰራተኛ ደንብ ልብስ
ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድር ለመሳተፍ የሚፈልጉ፡
- በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ድረስ በግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 102 በዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ15ኛው ቀን 8.30 ሰዓት ይከፈታል ሆኖም 15ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- ከላይ በሎት ቁጥር 1 የተገለጹ እቃዎች የጠቅላላ ሽያጭ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢዎች ብቻ መጫረት የሚችሉ መሆኑን፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ90 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 10,000 00 /አስር ሺህ ብር/ ብቻ በሲፒኦ ወይም አንኮንድሽናል ባንክ ጋራንቲ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ለ2 ወራት /60 ቀናት ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ባወጣው ግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 28/2010ና ጠቅላላ የውል ሁኔታዎች መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 102 ማግኘት ይቻላል፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ናሙና የተጠየቀባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ በቀረበው ድምር እቃዎች ላይ ከ2% በመብለጥም ሆነ በማነስም የቀረበ ድምር ስህተት ከጨረታ ውጪ ያደርጋል፡፡
- ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡– ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር በላይ/ ከሆነ ከቫት ተመዝጋቢዎች ላይ ቫቱን ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 046-221-24-71 04621262-26/
ፋክስ
046-21230-44.
በውሃ ማዕድንና ኢነርጅ ልማት ቢሮ