ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2013 በጀት ዓመት የጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ
- የጽሕፈት መሣሪያዎችን፤
- የፅዳት ዕቃዎችን፣
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን እንዲሁም
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣
- የሠራተኞች የደንብ ልብስ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ አቅራቢዎች የጨረታው ሰነድ በአንድ ላይ ተያይዞ ስለሚገኝ በዘርፉ የንግድ ፍቃድ ያላችሁና በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በንግድ ዘርፍ በ2012 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፣ በዕቃ አቅራቢዎች፣ ዝርዝር የተመዘገበ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ብር 3000 (ሦስት ሺህ ብር) ወይም በባንክ የተመሰከረ CPO ማቅረብ አለበት፡፡
- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በተከታታይ 5/12/2012 አየር ላይ ከዋለበት እስከ 25/12/2012 ቆይቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ5፡30 ላይ ታሽጎ በ7፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቦታ ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዶክመንት ወይም የጨረታ ሰነድ ከደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን የጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት ድረስ በአካል በመቅረብ በማይመለስ ብር 100 (መቶ) በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
- በአቅራቢዎች የሚቀርቡት ዕቃዎች ጥራታቸውንና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለበት፡፡
- በሚያቀርቡት የጨረታው ሰነድ ላይ የድርጅቱን ስም አድራሻ ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ መስፈር አለበት፡፡
- ለሚወዳደሩበት ዕቃዎች ከተጫራች የሚቀርበው ሰነድ የዕቃውን ዝርዝር ዓይነት፣ ስምና የተመረተበት ሀገር brande name እንዲሁም ዘመኑን የሚገልፅ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም የዕቃው ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ በደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን የጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት ጎሮ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ ኦሪጂናልና ኮፒውን ለይቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው በሚያቀርባቸው ዕቃ ላይ 10 ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡– መ/ቤቱ የሚገኘው በጂማ መስመር ሆኖ በወሊሶ እና በወልቂጤ መሃል ይገኛል፡፡ ወይም ከአ/አ 135 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ነው
ስልክ ቁጥር፡– 011-345-01-17 ወይም 011 3450 626/ 09 10 320898
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት