የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን የዱራሜ ዲስትሪከት ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ፕሮጀክቶችና ጥገና መንገዶች የሚያቀርቡ የውሃ ቦቴ እና የሰርቪስ መኪናዎች በጨረታ አፈጻጸም መመሪያ ላይ በዝርዝር በተገለጸው መሠረት ከህጋዊ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ አከራዮች በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
ሎት አንድ
- አይሱዙ
- ባለ 2 ጋቢና ፒክ–አፕ መኪና
- የሠራተኞች ማመላለሻ ሠርቪስ ሚኒባስ
- የውሃ ቦቴ
በዚህ መሠረት፡–እያንዳንዱን የመሣሪያ ዓይነት መጫረት የሚፈልገውን በመለየት
- ተጫራች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀትና በኣቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋናና አንድ ኮፒ «ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን በተለየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን የማይመለስ ብር 100.00/ አንድ መቶ በመከፈል ከዱራሜ ዲስትሪከት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ብቻ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ በዲስትሪክት ጽ/ቤት ድረስ በማቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ ጨረታው በዚያው ዕለት 8፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይታሸግና በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል ሆኖም ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከተው መሥፈርቶች መሠረት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋ 1 ከመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡ ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይት የለውም፡፡
- ተጫራች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታ ደንብና መመሪያ ውጪ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፣ ስልክ ቁጥር 0913183041/0468990312
በደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን
የዱራሜ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
ዱራሜ