ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደራ ወረዳ የአርብ ገበያ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት በ2012 በጀት ዓመት 2ኛ ቁጥር ጨረታ
- ለመጋዝን 3 እና ለመኖሪያ 2 አገልግሎት የሚሆኑ በአጠቃላይ 5 ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ 250.00 ብር በመክፈል ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በቢሮ ቁጥር 1 ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው የሚዘሩው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በ4 ሰዓት ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበትን ቦታ በተመለከተ በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው መነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት ከ15 በመቶ ያላነሰ በዝግ አካውንት በማስገባት በባንክ የተመሰከረለት ሰነድ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቁያ መለጠፊያ ሰሌዳ ላይ እና ከሚሸጠው ጨረታ ሰነድ ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ 058 287 01 28 መደወል ይችላሉ፡፡
በደራ ወረዳ የአርብ ገበያ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት