አስቸኳይ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2012
በየካ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 06 ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ27 ባለበጀት መስሪያ ቤቶች በ2012 በጀት አመት
- የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቋሚ እቃዎችን ኮምፒውተር፤
- ፕሪንተር፣
- ላፕቶፕ እና ስቴሽነሪ ወረቀት ፣
- ፍላሽ የመሳሰሉት
- የደንብ ልብስ አንጸባራቂ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የዕቃ እና አገልግሎቶች አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር መክፈል ግዴታቸውን የተወጡ፣ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆናቸውን
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ በሚጫረቱበት አይነት የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በየካ ክ/ ከተማ በወረዳ 06 ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ አዲሱ ህንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ ብር 2000( ሁለት ሺህ ብር ) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት ከላይ በተሰጠው ቢሮ የሚወዳደሩበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ የምታስገቡ ሆኖ በአምስተኛው ቀን ከቀኑ 5፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በእለቱ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በወረዳው አስተዳደር አንደኛ ፎቅ ከቀኑ 5፡30 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የቢሮ መገልገያ እቃዎች ቅድሚያ ናሙና ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች በሚያቀርቡበት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውንና ፊርማቸውን፣አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው
- የጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ባሸነፋት እቃ ዋስትና ውል ማስረከቢያ 2% ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታውን ለማሳሳት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ እንዲሆኑና ለወደፊት በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ እንደሚደረግ ያስያዙትን የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲወረስ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች ማጭበርበርና ሙስና (ጉቦ) መስጠት በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገውን የሚከበር መሆኑን ማረጋገጥ
ማሳሰቢያ:- ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡– 01118683636 መደወል ይችላሉ፡፡
በየካ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 06 ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ልዩ ቦታ ካሳንችስ ወደ አቧራ በሚወስደው መንገድ 28 ሜዳ ወንጌል ብርሃን ቤተ/ክርስቲያን አጠገብ፡፡
E-mail address woreda06Finance@gmail.com
የየካ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 06 ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት