የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር
001/2013 ዓ.ም
የወረዳ 09 የመጀመሪያ/ደረጃ ት/ቤት
- የደንብ ልብስ ፡
- አላቂ የትምህርት እቃዎች፣
- አላቂ የቢሮ እቃዎች ፣
- አላቂ የጽዳት እቃዎች፣
- ማስክ፤ ሳኒታይዘር ፤
- ፈሳሽ ሳሙና ፤
- የስፖርት መምህር ትጥቅ ፣
- የደንብ ልብስ ማሰፊያ ዋጋ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡
- የተጠቀሰው የሥራ ዘርፍ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውንና የምዝገባውን የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሚቀርበው አጠቃላይ ዋጋ ጋር 3000.00/ሶስት ሺህ ብር/ ማቅረብ የሚችሉ
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በተገለፀበት በ5 ቀን ውስጥ ውል መፈፀምና 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፣
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታውን ሰነድ ከት/ቤቱ ሂሣብ ክፍል የማይመለስ ብር 50.00/ሀምሣ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቶች በተመረጠው ናሙና መሰረት በ7 ቀን ውስጥ እቃዎቹን ለት/ቤቱ እቃ ግምጃ ቤት ክፍል ኃላፊ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ሠነዱ ላይ የተጠቀሱትን እቃዎች የሚሸጡበትን ዋጋና ሌሎች መረጃዎችን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እስከ ሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሁሉም ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተካተተ መሆን አለበት:: ጨረታው የሚታሸገው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ሲሆን በዛኑ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል። ት/ቤቱ በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው፡፡
አድራሻ፡– ኮተቤ ኪዳነምህርት መውጫ 300ሜ ገባ ብሎ የወረዳ 09 የመ/ደ/ት/ቤት
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0919320714
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትም/ቢሮ
በየካ ክ/ከተማ ትምህርት መምሪያ
የወረዳ 09 የመጀመሪያ/ደረጃ ት/ቤት