የጨረታ ማስታወቂያ
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ኢስተዳደር በ2013 በጀት ዓመት በ1ኛ ዙር ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ
- የተለያዩ ስቴሽነሪ አላቂ ዕቃዎች፣
- የፅዳት ዕቃዎች፣
- የደንብ ልብስ፣
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- ቋሚ ዕቃ፣ መስተንግዶ፣
- የቢሮ ዕቃ ጥገና፣ ፕሪንተር
- እና ፎቶ ኮፒ ቀለም በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች :
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ ፣ : የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 ብር (አንድ መቶ ብር) በመከፈል የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ።
- የሚያቀርቡት ዕቃ ዋጋ ከብር 30,000 ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ የቲኦቲ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- በጨረታ ላይ ያወጣናቸው ዕቃዎች በሙሉ ኦርጅናል እና ጥራቱን የጠበቁ ሆነው ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የጨረታ ፖስታ በሚያስገቡበት ጊዜ ለተወዳደሩበት ዕቃዎች ሳምፕል የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ያሸነፏቸውን ዕቃዎችን ስራሳቸው ትራንስፖርት መስሪያ ቤቱ ድረስ ማምጣት የሚችሉ።
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ብቻ የሚወዳደሩበትን ዋጋ ቫት በመጨመር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10 % የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጽ/ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን 10ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 11:00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታው ኣከፋፈት ላይ ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በወረዳው አስተዳደር ግቢ ውስጥ ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
አድራሻ፡መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ ወደ ኮተቤ በሚጨስደው መንገድ ቶፕ ቪው አጠገብ ያካ ተራራ ት/ቤት ፊት ስፌት ያለው የካ ክ/ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ስልክ ቁጥር፡-011646-70-06/0966-70-27-07
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት