አገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ ከመኖ ፋብሪካ ጋር ያለውን ተመጋጋቢነት በማየት የዱቄት ፋብሪካ አዋጭነት ጥናት ተጠንቶ እንዲቀርብ ወስኗል፤ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- የ2012 ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፤
- የ2012 ዓ/ም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያለው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፤
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ተጫራቾች ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከሰቆጣ ከተማ ዋግ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት የሃ/አስ/ር አ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ትችላላችሁ ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራች ያጠኑትን የአዋጭነት ጥናት ሰነዱን ዋናውንና ኮፒ ሁለት/2/ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00-4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ አስገብተው በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ዋና ጽ/ቤት የሃ/አስ/ርና ኦ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 2 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- ለበለጠ መረጃ፡–በስልክ ቁጥር 0335400837/0914602745 ወይም 0923439321 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/