የጨረታ ማስታወቂያ
በወልድያ ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽ/ቤት በአነስተኛ መስኖ መሰረተ ልማትና ቴክኖሎጂ መስፋፊያ የስራ ቡድን በ07/አደንጉር ገብኤል ቀበሌ የማመጫ ተ/ሃይማኖት ገዳም የፓምፕ መስኖ/pressurized irrigation project/ የግንባታ ስራ በተከዜ በጀት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የወልድያ ከተማ አስተዳደር የግዥና ፋይናንስ የስራ ቡድን በፋይናንስ የግዥ መመሪያ መሰረት ይህን የግንባታ ስራ ሊሰራልን የሚችሉትን ኮንትራክተሮች
- የመስኖ ግንባታው ሙሉ ወጭ በጨረታ አሸናፊ የሚሸፈን ሆኖና እንዲሁም ግንባታውን በተሰጠው ዲዛይን እና የስራ ዝርዝር መሰረት ገንብቶ ማስረከብ የሚችሉ፣
- በGC/በጀነራል ኮንስትራክሽን/ ወይም በWC/ዋተር ኮንስትራክሽን/ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው፣
- በተመሣሣይ የግንባታ ስራ /የፓምፕ መስኖ ስራ/የሰራ
- ከሰሩበት መስሪያ ቤት/ፕሮጀክት የመልካም ስራ አፈፃፀም ያላቸው፣
- የደረጃ 5/አምስት/ እና ከዚያ በላይ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች በአስቸኳይ ጨረታ ወጥቶ አሸናፊው ተለይቶ እንዲገለጽልን እንጠይቃለን፡፡
የወልድያ ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽ/ቤት