የጨረታ ማስታወቂያ
በወላይታ ዞን የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2012 ዓ.ም ለወረዳችን ውሃ ማዕድን ኢነርጂ ጽ/ቤት
- በLOT፤1 በጉልጉላ ቀበሌ ንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ እና
- በLOT 2 በቶሜ ጌሬራ ፤ በዋጭ ጋ ቡሻ ቀበሌ ንፁህ መጠጥ ውሃ ቦኖ የግንባታ እንዲሁም የቧንቧ መሥመር ዝርጋታ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች፡
- ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው የ2012 ዓ/ም ግብር በመክፈል ፈቃዳቸውን ያሳደሱና ተእታ (VAT)ተመዝጋቢ የሆነ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እስቴ ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ ፣ ከዞኑ ኮንስትራክሽን መምሪያ የተሰጠ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ በደረጃ WWC 6 እና ከዚያ በላይ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ከሚመለከተው ክፍል የተሰጠ ታክስ ክሊራንስ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በመንግሥት ግዥ ዕቃ አቅራቢነት ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ በባንክ በተረጋገጠ CPO LOT 1 ብር 20,000/ሃያ ሺ ብር/ እና ለLOT 2 ብር 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራች የመልካም የሥራ አፈጻጸም ላለፉት ሦስት ዓመት በበጀት ዓመት በተመሳሳይ ሥራ ቢያንስ ብር 1,000,000/አንድ ሚሊዮን ብር/ ርክክብ ቨርቫልና የሥራ ውል ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዶክመንቱ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ መጥተው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ፋይናሻል እና ቴክኒካል ዶክመንት እያንዳንዳቸው አንድ ኦሪጅናል ሁለት ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 15 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት በወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብ ስርዝ ድልዝ ያለ መሆን የለበትም፡፡
- ተጫራቾች በዞኑ ውስጥ ሲሠሩ ምንም ዓይነት ማስጠንቀቂያ ያልተሰጣቸው መሆን አለባቸው፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 046-180-6026 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ
በወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት