ማስታወቂያ የጨረታ
በወላይታ ዞን የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2012 ዓ.ም ለወረዳችን ሚሊሽያ ጽ/ቤት በመደበኛ ፕሮግም ከተያዘው በጀት ለሚሊሻ አባላት የመከላከያ ሬንጀር ደንብ ልብስ፣ ቀበቶ፣ መለዮ እና ጫማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች፡
- በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር ከፍሎ ያጠናቀቀ፡፡
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡
- VAT (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
- TIN(ቲን)የመለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል፡፡
- በዋጋ ማቅረብያ ላይ ማህተም፤ ፊርማ፣ ቀንና ዓ/ም በግልጽ መጻፍ አለበት፡፡
- በዘርፉ ዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የተወዳደሩበት ዕቃ ናሙና በዕለቱ ይዞ የቀረቡት ብቻ ይወዳደራሉ፡፡
- አሸናፊ በሆኑበት ዕቃ አቅርቦት በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ስምምነት ውል ለመግባት ፍቃደኛ ካለሆኑ ያስያዙት ሲፒኦ ብር ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
- ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 10,000.00/አሥር ሺህ/ ብር በባንክ በተመሰከረ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታው ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ለእያንዳንዱ ዶክመንት የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከሶዶ ዙ/ወ/ገቢዎች ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሣጥን ጋዜጣው ከወጣበት 15 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡– ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-180-6026 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡
የወላይታ ዞን የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት