ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/ኢወ/ኢ/ል/ጽ/ቤት 69/13
በወላይታ ዞን አበላ አባያ ወ/ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል በዓመታዊ የግዥ ዕቅድ መነሻ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩ ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን በዘርፉ ከተሰማሩ እቅራቢዎች ዓመታዊ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1. የጽሕፈት መሣሪያዎች
- ሎት 2.የሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት 3. የኤሌክትሮኒክ ዕቃዎች
- ሎት 4. ቋሚ እቃዎች
ስለዚህ ተጫራቾች፡
- በየዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፊኬት፣ የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ (ቲን) ሰርተፊኬት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራች የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ብር በየሎቱ የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1 እና 2 ለእያንዳንዱ ብር 20,000 ሃያ ሺህ ሲሆን ለሎት 3 እና 4 ለእያንዳንዱ ብር 25,000 /ሃያ አምስት ሽህ/በኢትዮጵያ ባንከ እና በሌሎች በግል ባንኮች በጀርባው የባንኩ ማህተም የተረጋገጠ ጋራንቲ ሲፒኦ ወይም በመ/ቤቱ የግቢ ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከኦሪጅናል የጨረታ ሀሳብ ሰነድ ጋር ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በሰም ታሽገው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች አንዱን ዕቃ እና አገልግሎት ዋጋ የሚያቀርቡበትን የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን ስታሸገ ፖስታ ሙሉ አድራሻ የድርጅቱ ስም ፊርማና ማህተም በማድረግ በጨረታ ሰነድ ላይ በተዘጋጀው ዋጋ መሙያ ሠንጠረዥ በመሙላት በአ/አ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን በጨረታ አዳራሽ መክተት ይኖርባቸዋል።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ በ8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመምሪያው የጨረታ አዳራሽ ይከፈታል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች አስፈላጊውን ውለታ በመፈጸም ሙሉ በሙሉ በአ/አ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ በማቅረብ ገቢ ሲያደርጉ እና መ/ቤቱ የሚገዙትን ዕቃዎችን ገቢ መሆኑን ሙሉ በሙሉ ሲያረጋግጥ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0916406324/ 0913857603 እና 0913336712 /0916719687 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በወላይታ ዞን አበላ አባያ
ወ/ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት