ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የማስታወቂያ ቁTir መደበኛ 02
በወላይታ ዞን በዳሞት ሶሬ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በ2013 ዓ.ም በመደበኛ በጀት ከተለያዩ መ/ቤቶች በቀረበው ጥያቄ መሠረት
1ኛ መስተንግዶ
2ኛ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
3ኛ ሞተር ሳይክል
4ኛ የመኪና ጥገና
5ተኛ ደንብ ልብስ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡
ስለዚህ፡
ሀ/ በዘርፉ ሕጋዊ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣
ለ/ የTIN ተመዝጋቢ እና የVAT ተመዝጋቢ የሆኑ፣
ሐ/ የአቅራቢነት ምስክር ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
መ/ ከሚያገኘው የተጣራ ሽያጭ በፋይ/ደንብ መሠረት 2% ለመከፈል ፈቃደኛ የሆነ ፣
ሠ/ ለጨረታው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ ለእያንዳንዱ ሰነድ CPO ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር /ማስያዝ የሚችል ፣
ረ/ አሸናፊ መሆኑ ሲረጋገጥ ውል ገብተው ዳ/ዕ/ወረዳ ፋይናንስ ድረስ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ፣
ሰ/ አመልካቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱ ስም ፣ሙሉ አድራሻ ፣ ፊርማ ፣ ማህተምና ስልክ ቁTir መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡
ሸ/ተጫራች አሸናፊ ሲሆን ውል ገብቶ የሚያቀርባቸው ከመስተንግዶ ግዥ ወጪ ዕቃዎች በዘርፉ ባለሙያ ተረጋግጦ ክፍያ የሚፈፀም ይሆናል ::
ስለዚህ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ30 ቀናት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 50.00 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ከዳሞት ሶሬ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁTir 6 ቀርበው ሙግዛት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው 30 ተከታታይ ቀን አልፎ ቀጣይ በሚውለው በሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 5፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፦
- የተጫራቾች ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም ::
- የውል ማስከበሪያ ሲያስይዙ የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ ሲሆን ዕቃውን ሲያስገቡ የውል ማስከበሪያ ተመላሽ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻስ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሱ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁTir 0462720412/0913921119 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ::
በወላይታ ዞን በዳሞት ሶሬ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት