የጨረታ ማስታወቂያ
- በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በሶዶ ከተማ አስተዳደር ሥር ለሚገኙ ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት-1. የጽ/መሳሪያ
- ሎት–አልባሳትና የቆዳ ውጤቶች(ደንብ ልብስ)
- ሎት-3.የእንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶች(ፈርኒቸር)
- ሎት-4.የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- በመሆኑም በሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች የተመዘገቡ፣ ለ2013 በጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
- ጨረታው የሚከናወነው፡– ሀገራዊ ሽፋን ባለው ሚዲያ(በአዲስ ዘመን ጋዜጣ) ለ15 ቀናት አየር ላይ በሚቆይ ማስታወቂያ ጥሪ ተደርጎ በክልሉ የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 28/2010 አንቀጽ 16 (የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አሠራርን) በመከተል ይሆናል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች መረጃዎችን ለማግኘትና የጨረታ ሰነዱን ለማየት ጨረታው ኣየር ላይ በሚውልባቸው የሥራ ቀናት ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ረፋድ 6፡30 እና ከቀኑ 7፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የወላይታ ሶዶ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ጉዳይ ቡድን ቢሮ ቀርበው ማነጋገር ይችላሉ።
- የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100.00(አንድ መቶ ብር) በሶዶ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት መደበኛ አካውንት አካውንት ቁጥር 1000018212335 ገቢ ያደረጉበትን ስሊፕ በማቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ፡–የወላይታ ሶዶ ከተማ ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ጉዳይ ቡድን ቢሮ
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይቻላል። ዘግይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል።
- ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ሌሎች መገኘት የሚፈልጉ ባሉበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽገው በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል። 16ኛው ቀን የበአላት ቀን ከሆነ (የሥራ ቀን ካልሆነ) በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች በድርጅቱ ስም የተዘጋጀውን የጨረታ ዋስትና
- ለሎት1-.(ለጽ/መሳሪያ ግዥ) 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ኢት.ብር) ፣
- ለሎት-2.(ለአልባሳትና የቆዳ ውጤቶች ለደንብ ልብስ ግዥ) 20,000.00(ሃያ ሺህ ኢት.ብር)፣
- ለሎት-3(ለእንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶች (ለፈርኒቸር ግዥ )15,000.00(አሥራ አምስት ሺህ ኢት.ብር) እና
- ለሎት4(ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ) 30,000.00(ሰላሳ ሺህ ኢት.ብር) በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- በግዥ መመሪያ 28/2010 አንቀጽ 16.25.2 መሠረት ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ውል ለመፈራረም ሲቀርብ ቢያንስ የውሉን ዋጋ 10 %(አሥር በመቶ) በውል ማስከበሪያነት ለመ/ቤቱ የማስያዝ ግዴታ አለበት።
- ርክብክብ የሚፈጸምበት ቦታ ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ አስተዳዳር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ይሆናል።
- መ/ቤታችን የጨረታውን ሂደት በሙሉም ሆነ በከፊል እንዲሁም በማንኛውም ጊዜ የማራዘም ወይም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ 0916-34-98-25/09107929-39 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
በወላይታ ዞን በሶዶ ከተማ አስተዳደር የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ዋና ጽ/ቤት