የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ጀሞ/01/2013
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 04 ስር የሚገኘው ጀሞ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በተለያዩ ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች ማለትም:
- ሎት 1. የፅህፈት አላቂ ዕቃ
- ሎት 2. የቢሮ አላቂ እቃ
- ሎት 3. የፅዳት አላቂ ዕቃ
- ሎት 4. የደንብ ልብስ
- ሎት 5. የላብራቶሪ ዕቃ
- ሎት 6. የኮምፒዩተር እና ማሽነሪ ጥገና አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ከተ/ቁ 1-6 በተጠቀሱት ዕቃዎች አግባብነት ያለው ዋና የታደሰ የንግድ ፍቃድ የግብር መክፈያ ቁጥር ያላቸው እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የዘመኑን ግብር ከፍለው እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በአዲስ አበባ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ በወረዳ 04 በጀሞ የመጀ/ደ/ት/ቤት በመገኘት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 2000 (ሁለት ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሰነዱን ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ በተለያየ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች እያንዳንዱ የሚሸጡበትን ዋጋና የጠቅላላውን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመግለፅ በታሸገ ፖስታ ገቢ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታ ዓይነት በመጥቀስ ከጀሞ የመጀ/ደረጃ ት/ቤት ገቢ ማድረግ አለባቸው::
- ተጫራቾች ለሚጫረቱት ዕቃ ናሙና አብሮ ማቅረብ አለባቸው::
- . ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተረጋገጠ በኋላ የውል ማስከበሪያ ሲፒዮ ማስያዝ አለባቸው::
- ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጀሞ የመጀደ/ት/ቤት ላይብረሪ አዳራሽ ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ :- ዓለም ባንክ ጀሞ የመጀ/ደ/ት/ቤት ስልክ ቁጥር ፡- 0118-35-30-56 / 0118-35-30-46
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 04 ስር የሚገኘው ጀሞ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት