የጨረታ ማስታወቂያ
በኮቀ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የረጲ ሁለተኛ ደርጃ ት/ቤት በ2013 ዓ.ም የስራ ዘመን ከዚህ በታች በሎት የተደራጁ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት፡– 1 የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች
- ሎት፡– 2. የፅዳት እቃዎች
- ሎት፡– 3. የደንብ ልብሶች
- ሎት፡– 4. የላብራቶሪ እቃዎችና መጽሐፍት
- ሎት፡– 5. የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮች እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
በዚህ መሰረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር በመክፈል/ የጨረታ ሰነድ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ወርዳ 02 አለፍ ብሎ ካራ ቆሬ አካባቢ አጃንባ መውጫ ቢሮ ቁጥር 08 ቀርበው መውሰድ እንደሚችሉ እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
- የግብር ከፋይነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ /ባት ተመዝጋቢዎች መሆን አለባቸው።
- የሚቀርበው የዋጋ ሰነድ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት::
- ተጫራቾች ጨርታው ሲከፈት የጨርታ ማስከበሪያ የሚሆን።
- ሎት 1፡– 8,806 /ስምንት ሺህ ስምንት መቶ ስድስት ብር
- ሎት 2: -5,000 /አምስት ሺህ ብር
- ሎት 3:- 10,000 /አስር ሺህ ብር
- ሎት 4- 400 /አራት መቶ ብር
- ሎት 5 3,800 /ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊው ተጫራች በሰነዱ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል መዋዋል አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ሰነድ ዋናውና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በማድርግ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።
- አሸናፊ ድርጅት ያሽነፈበትን እቃ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ያላቀረበ ድርጅት ከውድድሩ ውጭ ይሆናል። እቃው በናሙናው ላይ ያለውን የጥራት ደርጃ ይዞ ካልተገኘ ተመላሽ ይሆናል።
- ገዢው በአካል የሚገዛውን ዕቃ እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
- ለአሸናፊ ተጫራቾች በሰነድ ውስጥ የተካተተውን ጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም እስከ አስር ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ ከፍለው ውል መዋዋል ይችላሉ።
- ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸው እቃዎች በወቅቱ ማቅረብ ካልቻሉ ያስያዙት ሲፒኦ ይወረሳል/ተመላሽ አይደረግም።
- የእቃ ማስረከቢያ ቦታ ረጲ 2ኛ ደርጃ ት/ቤት ይሆናል።
- በሚቀርበው የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ የድርጅቱ ሃላፊ ስምና ፊርማ የድርጅቱ አድራሻና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት።
- ት/ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ ስድስት ወር ውሉን ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለሚቆጠር አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ11ኛው ቀን ጠዋት 5:00 ሰዓት ታሽጎ 5:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በረጲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሒሳብ ክፍል ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
- የእቃ ማጓጓዛ ብር አሸናፊው ተጫራች ይሸፍናል።
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ በኮ/ቀ/ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የረጲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ ሲሆን፣
ስበስጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 348 88 50/ 011 347 18 16 እና 011 369 41 56
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ትምህርትና ሥልጠና ጽ/ቤት የረጲ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት