የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2013
በኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ ወረዳ 15 ቃሌ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ2013 በጀት ዓመት ከዚህ በታች ከሎት 1 እስከ ሎት7 የተከፋፈሉ ግዥዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት ቁጥር |
የሚገዛው ዕቃዎች/ጥገና አገልግሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን (CPO) |
ናሙና
|
ሎት 1 |
አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች |
5000 CPO |
ማቅረብ አለባቸው |
ሎት 2 |
የደንብ ልብስ |
4000 CPo |
ማቅረብ አለባቸው |
ሎት 3 |
አላቂ የጽዳት ዕቃዎች |
3000 CPO |
ማቅረብ አለባቸው |
ሎት 4 |
ቋሚ ዕቃዎች |
3000 CPo |
በፎቶ ማቅረብ አለባቸው |
ሎት 5 |
ቤተ–ሙከራ |
1500 CPO |
ማቅረብ አለባቸው |
ሎት 6 |
የህትመት ስራ |
1500 CPO |
አያስፈልግም |
ሎት 7 |
የጥገና አገልግሎት |
1500 CPO |
አያስፈልግም |
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሱ ደርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡
- በዘርፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ የቫት (VAT) ተመዝጋቢነቱ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ ወረዳ 15 ቃሌ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ 22/3/2013 ዓ.ም ከወጣበት ቀን እስከ 6/4/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው 11ኛ ቀን ማለትም 6/4/2013 ዓም በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን በመሙላት ዋናውን እና ኮፒ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን፣ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ በመፈረም ማቅረብ አለባቸው፣ ሰነዶቹ በማህተም መረጋገጥ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዕቃዎች ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎችን ናሙና ግልጽ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የግዥ ውል በሚፈጸምበት ጊዜ ሰነዱ ላይ የተሰጠው የዕቃ ብዛት 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ ኣውቆ የመጫረት ግዴታ አለበት፡፡
- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ:- ቃሌ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እስኮ እያሱ ፀበል በአከሱም አዳራሽ 150 ሜትር ገባ ብሎ
- በተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁ 011 2 73 17 69
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ሥልጠና ጽ/ቤት
የቃሌ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት