Cleaning and Janitorial Equipment and Service / Computer and Accessories / Equipment and Accessories / Garments and Uniforms / Installation / Laboratory Equipment and Chemicals / Machinery / Maintenance and Other Engineering Services / Materials / Office Furniture / Office Machines and Accessories / Others / Printing and Publishing / Stationery / Textile

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ አስተዳደር የሠላም በር እና አጸደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መመሪያ መ.ቁ 02/13

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ አስተዳደር የሠላም በር እና አጸደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት

 • የሚያገለግሉ እቃዎችን ወይም አላቂ የፅህፈት እና የቢሮ እቃዎች፤
 • አላቂ ፅዳት እቃዎች፤
 • የአስተዳደር ሠራተኞች የደንብ ልብስ፤
 • የተለያዩ የህትመት ስራዎች፤
 • የላቦራቶሪ እቃዎች፤
 • አጋዥ መፅሃፎች፤
 • የማሽነሪ ጥገና እና
 • የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በዘርፉ የተሠማራችሁ ህጋዊ ነጋዴዎች በጨረታ አወዳድረን በቴከኒከና እናበዋጋ በማወዳደር እሸናፊ ከሆኑት ድርጅቶች ለመግዛት የምንፈልግ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
 1.  ተጫራቾች የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው የዕቃአቅራቢዎች ዝርዝር እና በገቢዎችና ጉምሩከ ባለስልጣን የተጨማሪእሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች የ2012 ዓ.ም ግብር የከፈሉና ለ2012 ዓም የታደሠ የንግድ ፍቃድ መሆኑን የሚገልፅ አግባብነት ያለው ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮበ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ከሰዓት 7፡30-11፡30 ሰዓት የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ በሠላም በር አጸደ ህፃናትናየመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከፍያና ሂሳብ አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት በመቅረብ የማይመለስ 100 ብር መቶ ብር / ከፍለው መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ የእቃዎችን ዝርዝር ዋጋ እና አይነት በመግለፅ በታሸገ ኢንቨሎፕ በግዢ ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግይኖርባቸዋል፡፡ ፖስታው ካልታሸገ አይከፈትም ወይም ለውድድር እይቀርብም ::
 4. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10የስራ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ11 ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛውቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል ፡፡ (ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል)
 5.  ተጫራቶች ሌላው ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ተንተርሰው ዋጋ መስጠት አይችሉም፡፡
 6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የሚያቀርቡት የእቃ አይነት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበት፣ ስልጣንባለው አካል የተፈረመባቸው የተሟላ አድራሻቸውን የሚገልጽና ህጋዊ ማህተብ ያረፈበት ሊሆን ይኖርበታል፡፡
 7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የእቃ ዋጋ ፣ የዕቃውን አይነት/ብራንድ/፣ እቃው የተመረተበት ሀገር በግልፅ መጥቀስ ይኖርባቸዋል እንዲሁም ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚያቀርቡት እቃዎች ናሙና ወይም ሳፕል ማቅረብ፣ የፕሪተር እና የኮፒ ቀለሞች ኦርጅናል ትክክለኛነት/ የማረጋገጫ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡
 8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ብር 5000 /አምስት ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO በት/ቤቱ ስም በማሰራት ከጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሠዓት በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸው አካል የጨረታ ማስከበሪያ ደብዳቤ በት/ቤቱ ስም ማለትም ሠላም በር አጸደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በሚል አፅፈው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 9. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ የዋጋለውጥምሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም በተወዳደሩት ዋጋ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው የውል nማስከበሪያ 10% ለግዥ ፈፃሚ አካል ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው በውል መሠረት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ከተወጡና ውሉን ተመላሽ ሲያደርጉ ነው::
 10. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለጸበት በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል ካልተዋዋለ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
 11. በጨረታው ያሸነፉት ጫራቶች ለአሸነፉአቸው ዕቃዎች ውል ከተዋዋሉበት ቀን ጀምሮ በአስር ቀን ውስጥ በራሳቸው የትራንስፖርት ፣ የማስጫኛ እና የማስወረጃ ወጪ በመከፈል በሠላም በር አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል። እቃዎቹን ገቢ የማያደርጉ አሸናፊነት ተጫራቶች ያስያዙት የውል ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡ በተጨማሪ በህግ የሚጠየቁበትስርዓት እንፈጥራለን፡፡
 12. ት/ቤቱ አሸናፊው ተጫራች ከመረጡ በኋላ በሚገዙት እቃዎች ብዛት መጠን ላይ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20% የመቀነስ ወይም የመጨመር መብታቸው የተጠበቀ ነው ::
 13. ተጫራቶች በጨረታው የአፈጻጸም ሂደት ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጅቁጥር 649/2001 አንቀፅ 51፣53 እና 54 እንዲሁም በመንግስት ግዥ አዋጅ አፈጻፀም መመሪያ አንቀፅ 43 መሠረት አቤቱታ የማቅረብ መብታቸው እንደተጠበቀነው፡፡
 14. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
 15. በጨረታው ሰነድ ግለፅ ያልሆኑ ጉዳዮች ካሉ ውጤት ከተገለፀበትቀን ጀምሮ ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ውስጥ በአካል በመቅረብ ሠላም በር አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 16. ት/ቤቱ ባዘጋጀው ቅፅ ወይም የዋጋ ማቅረቢያ በስተቀር በሌላ ቅፅ መሙላት አይቻልም፡፡
 17. ንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅፁን ሲሞላ 15 % ቫትንበመጨመር ይሆናል፡፡ 15% ቫትን ያላካተተ ተጫራች ለውድድርአይቀርብም፡፡
 • አድራሻ፡- በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ10 ሉካንዳ ታክሲ ማዞሪያ ወደፌዴራል ፖሊስ ማስልጠኛ ተቋም በሚወስደው አስፓልት በስተቀኝ በኩልሰዋሰው ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ጎን
 • ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-2-73-90-95/ 011-2-79-14 68//011-8-29 07-46 ይደውሉ

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ አስተዳደርየሠላም በር እና አጸደ ህፃናትና

የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት