የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሙሲፋ/12/2012
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አንድ ዶዘር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100.00 ከቫት በፊት በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ጠመንዣ ያዥ አጠገብ የሚገኘውን ጋራድ ሞል ሦስተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 432-38 ከሚገኘው የአቅርቦት አገልግሎት ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች በጨረታ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ ብር 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በአቅርቦት አገልግሎት ቢሮ ይከፈታል፡፡
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ፡-0114420216
ፋክስ፡-0114420688
አዲስ አበባ
በኬሚካል ኢንዱስትሪ
ኮርፖሬሽን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ