የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሙሲፋ/11/2013
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለ2013/4 በጀት ዓመት ከጅቡቲ ወደብ እስከ ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ድረስ 91,000 ቶን ድንጋይ ከሰል (Coal) ለማጓጓዝ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማስራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 115.00 (አንድ መቶ አስራ አምስት ብር) ተጨማሪ እሴት ታክስ (ጨምሮ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት ጋራድ ህንጻ ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የአቅርቦት አገልግሎት ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ::
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CP0. ከቴክኒክ ዶከመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በአቅርቦት አገልግሎት ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በእለቱ Tir 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በአቅርቦት አገልግሎት ቢሮ ይከፈታል፡፡ ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
ስልክ ቁጥር፡- 0114420216
ፋከስ፡- 0114420688
አዲስ አበባ
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን
የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ