የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሙሲፋ/16/2012
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን በሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል Cabon Brush በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100.00 ከቫት በፊት በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ሕንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የአቅርቦት አገልግሎት ቢሮ እየቀረቡ መገግዛት ይችላሉ:: ተጫራቾች ለጨረታ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ ብር 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በአቅርቦት አገልግሎት ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በአቅርቦት አገልግሎት ቢሮ ይከፈታል፡፡ ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::