ጨረታ ማስታወቂያ
በከምባታ ጠምባሮ ዞን የዱራሜ ከተማ አስ/ር 2012 በጀት ዓመት ከሚያሰራቸው የህንፃ ሥራዎች Package number /Durame UllDP CW-024/2019/20 የሆነውን G+5 ህንጻ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት. GC 5-BC 4 እና ከዚያ በላይ ደረጃ ያላቸው ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፤
- ተጨራቾች በየዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የአቅራቢነት፤ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት እና ቲን ነምበር ማቅረብ የምትችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 350,000.00/ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችል፡፡
- በየዘርፉ የተዘጋጁትን የጨረታ ሰነዶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 500.00 ብር/አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በማድረግ የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ31ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡31ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0465540458
የዱራሜ ከተማ አስ/ር ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት
ግዥ ን/አስ/ር የሥራ ሂደት
ዱራሜ