ከባድ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ብዛታቸው 25 የሆነ ከባድ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
- ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው መመሪያ መሰረት በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተጠቀሰውን ተሽከርካሪ ህጋዊ አስመጪ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በቅድሚያ የሚያቀርቡትን ተሽከርካሪ ዋጋ 2% የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ በባንክ የተመሰከረለት CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ሌላው በሚያቀርበው የጨረታ ዋጋ ላይ በመንተራስ በፐርሰንት አሳንሶ ወይም አስበልጦ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም::
- ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/ አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00-11፡00 እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰአት አዳማ ሶደሬ መንገድ ከሚገኘው ዋናው መ/ቤታችን ወይም አዲስ አበባ ሳሪስ ካዲስኮ ህንፃ ፊት ለፊት ከሙለጌ ህንፃ ወረድ ብሎ ከሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤታችን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በግንባር በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይኖርበታል፣
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/ አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00-11፡00 እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰአት አዲስ አበባ ካዲስኮ ፊት ለፊት በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤታችን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፣
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ከ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት 8፡00 ሰአት እረስ አዳማ ሶደሬ መንገድ ከሚገኘው ዋናው መ/ቤታችን መሰብሰቢያ አዳራሽ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዳችሁን ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማስገባት ይኖርባችኋል፣የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ አዳማ ሶደሬ መንገድ ከሚገኘው ዋናው መ/ቤታችን መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፣
- የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5/አምስት/ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ከግዥ ጋር የተያያዙ ውሎችን ይፈራረማል፣
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ይመለስላቸዋል፣
- አ/ማህበሩ የተሻለ አማራጮችን ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 022-111 17 91 ናዝሬት 011442 27 11 ወይም 0114-43 13 48 ይደውሉ::
በከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር