የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2013
በአብክመ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የጅ/ጥ/ወረዳ ገንዘብና ኢኮ/ትብብር ጽ/ቤት ሰንበቴ ከተማ ከአዲስ አበባ በደሴ ከተማ መስመር በ265 ኪ/ሜ ላይ የምትገኝ ሲሆን፡– በወረዳው ላሉ
- መኪናዎች ስፔርፓርት እና
- የደንብ ልብስ በመደበኛ በጀት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ በዘርፉ የተሰማሩ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ንግድ ፈቃድ፣ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /Tin no/ እና የVAT ተመዝጋቢ ደረሰኝ ያላቸው መሆን አለበት፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ለተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 20/ሃያ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከጅ/ ጥ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 5 በ25/2/2013 ዓ.ም መግዛት ይችላሉ፡፡ በጨረታው ሰነድ ላይ ዝርዝር ማብራሪያዎችን ያገኛሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ በታሸገ ፖስታ የአቅራቢውን የባለቤት ስምና አድራሻ የሚገልፅ ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት እስከ 5/3/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ጅ/ጥ/ወ/ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢቁ. 5 ማስገባት አለባቸው፡፡ በዚሁ እለት 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5/3/2013 ዓ.ም 8፡15 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
- ጨረታውን በተናጠል የምናወዳድር መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች ለሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 1% CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ቢሮ ቁጥር 4 ደረሰኝ በመቁረጥ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0331180322/37 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የጅ/ጥ/ወረዳ
ገንዘብና ኢኮ/ትብብር ጽ/ቤት