አንደኛ የጨረታ ማስታወቂያ
የአፈፃፀሙ ከሳሽ ዘርፉ ታደሰ እና የአፈፃፀም ተከሳሽ ኢንቴል ኤልሳሜክስ ጆይንት ቬንቸር ነቀምቴ መካከል ያለውን ክርክር በተመለከተ የተከሳሹ አፈፃፀም በአሁኑ ጊዜ በምስራቅ ወለጋ ዞን በጉቶ ጊዳ ወረዳ በኡኬ ቀበሌ አስተዳደር ውስጥ የሚገኘውን ተገምቶ የቀረበ ባለ 39 ብሎክ ቤት በመነሻ ዋጋ 15,115,226.89 /አስራ አምስት ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ሃያ ስድስት ብር ከ89/100 ካት የተሰኘ ግሬደር ማሽን 1200 ኤች የአንዱ መነሻ ዋጋ 2,120,300.40 /ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ ሃያ ሺህ ሶስት መቶ ብር ከ40/100 አንድ የኮንክሪት ፓንች ማሽን ዋጋው ብር 5,250,143.65 /አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሣ ሺህ አንድ መቶ አርባ ሶስት ብር ከ63/100 የባለእዳው አፈፃፀም ንብረት ግልጽ በሆነ ጨረታ በ17/4/2013 ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ እስከ 6፡00 ሰዓት ስለሚሸጥ መግዛት የሚፈልጉ ካሉ ንብረቱ የሚገኝበት ስፍራ ድረስ ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምዕራብ
ምድብ የፍትሐብሔር ችሎት