1ኛ ግዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልዕ በባሌ ዞን የጎባ ከተማ ገ/ኢ/ት/ ጽ/ቤት በ2013 ዓም በጀት 1ኛ ዙር ለጎባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አሽዋ ለማምረት እስካቫተር ማሽን ኪራይ እና በጎባ ከተማ ወስጥ ለውስጥ መንገድ
- በተለያዩ ቦታዎች አሽዋ ለማስደፋት በኪራይ መልክ ባለ 16 M3 ሜትር ኪዩብ በላይ (M3) የሚጭን ገልባጭ ዳምትራክ በመከራየት አሸዋ ለማምረትና ለማስደፋት በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በዘርፉ ባገልግሎት ሰጪነት የተሰማሩ በውድድሩ ላይ እንዲካፈሉ እየጋበዝን በውድድሩ ላይ ለመካፈልቀጥሎ የቀረቡትን መመዘኛዎች ወይም መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ቲን ነምበር ተዘጋቢ መሆኑንና የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸወና ፎቶ ኮፒውን ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ የሚችል ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮው ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመግዛት ከጎባ ከተማ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6:30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 እስከ 11፡30 ሲሆን 100 (አንድ መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ Acc.No 1000028126712 በማስገባት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠድ ዋናውን እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት 16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 (ሶስት ሰዓት ከሰላሳ )የጨረታው ሠነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ከታሸገ በኋላ በዚሁ ዕለት በ4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የእስከቨተር ማሽን እና የገልባጭ ዳም ትራክ ሙሉ ወጭውን በመቻል ባከራዩ እንደሚሸፈን አወቀው መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡
- የኪራዩን ዋጋ መ/ቤቱ የሚከፍለውኑ በውሉ መሰረት ሙሉ በመሉ ሥራውን በጥያቄው መሠረት ማለቁ ሲረጋገጥ ብቻ ነው::
- ተጫራቾች በቀረበው እስፔሲፊኬሽን መሰረት ጨረታውን ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸ ው ቀን በኋላ መስሪያ ቤቱ ቀርበው ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል በተጨማሪም ውል ከገቡ በኃላ ሥራውን በውሉ መሰረት ሰርተው መጨረስ አለባቸው::
- የግልባጭ ዳም ትራክ ኪራይ እና አሸዋ ለማምረት ኤስከቨተር ማሸን 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ በሲፒኦ / ብቻ CPO /ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የግልባጭ ዳም ትሪክ ኪራይ እና አሸዋ ለማምረት ኤስካቨተር ማሽን የውል ማስከበሪያ የሥራውን ሙሉ ዋጋ 10% (ፐርሰንት) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ጎባ ከተማ ገ/ኢ/ት/ ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 0226612764 መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን የጎባ ከተማ
ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት