የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የጮሌ ወረዳ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በ2013 የበጀት ዓመት ለማሰልጠኛ የሚሆኑ መሣሪያዎች
- የፅህፈት መሳሪያዎች ፤
- የህንፃ መሣሪያዎች ፤
- የእንስሳት ህክምና መሳሪያዎች ፤
- ኮምፒዩተሮች እና
- የኮምፒዩተር እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎችን ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
- የዘርፉን ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የ2012 ዓ.ም ግብር የከፈሉ እና የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፡፡
- በፌደራል ወይም በክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የቲን ነምበር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ(VATተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን ማካተት አለማካተታቸውን መግለጽ አለ ባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15ተከታታይ የስራ ቀናት በጮሌ ቴ/ሙ/ማሰልጠኛ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተራ ቁጥር 5 በተጠቀሰው ቀናትና ቦታ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በ 15 ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛኑ ዕለት ከሰዓት8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ካቀረበው ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000/አምስት ሺ ብር ብቻ በባንክ የተረጋገጠ(CPO) በጮሌ ቴ/ሙ/ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ስም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በእጅ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተሸናፊ ተጫራች ለጨረታ ያስያዘውን ብር ወዲያውኑ ይመለስለታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎቹን በራሱ ማጓጓዣ ወጪ ጮሌ ቴ/ሙ/ማሰልጠኛ ኮሌጅ መቅረብ አለበት፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃ፡ ቁጥር፡-0920376938/ 0932113459/ 0920080762 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአርሲ ዞን ጮሌ ወረዳ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ