የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን የባቱ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2013 በጀት ዓመት ጠቅላላ የዓመቱን የግዢ ፍላጎቶችን ሆስፒታሉ በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ግለሰቦች በማወዳደር ከአሸናፊው መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የሥራ ፍቃድና የዘመኑን ግብር መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ 5000.00 ( አምስት ሺህ ብር ) ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው መወዳደሪያ ኦርጅናልና አንድ የኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች ከተፈላጊ መረጃዎች ጋር ተያይዘው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በአንድ ፖስታ ይቀርባል::
- የጨረታው ሰነድ በኦሮሚያ ክልል በባቱ አጠቃላይ ሆስፒታል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 የሥራ ቀናት አየር ላይ ይቆያል ፣ ለአንድ ሰነድ የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ) ብር በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ ሰነዱ የያዘው
4.1. የግዥ ዓይነቶች :
- መድኃኒት ፣
- የህትመት ሥራዎች፣
- የጽሕፈት መሣሪያ ፣
- የፅዳት እቃዎች ፣
- የኦክስጅን ስልንደሪ መሙላት፣
- የሠራተኞች የደንብ ልብስ ፣
- የጥበቃ አገልግሎት ሥራ፣
- የፅዳት አገልግሎት ሥራ፣
- የታማሚዎች ምግብ አቅርቦት እና የተለያዩ ግዥዎች፡፡
5. ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ከሆስፒታሉ ግዥ እና ፋይናንስ ክፍል 100 ብር (አንድ መቶብር ) በመግዛት መሙላት ይችላል፡፡
6. ጨረታው በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ በመቅረብ ጨረታውን የያዘ ሳጥን በዚያው ዕለት 4፣30 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
7. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪል በሰዓቱ ባይገኙም የጨረታው ሣጥን ከመከፈት አያግድም፡፡
8 ተጫራቾች ዋጋ ቫት( VAT ) ወይም (TOT ) ብለው መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ካልተጠቀሱ ታክስን እንዳልተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል ፡፡
9. ሆስፒታሉ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፣ 0913368618/ 0930106935 መጠየቅ ይቻላል፡፡
በኦሮሚያ ጤና ቢሮ የባቱ
አጠቃላይ ሆስፒታል