የጨረታ ማስታወቂያ ቁ 1/2013
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከምዕራብ ሸዋ ዞን የአድአ በርጋ ወረዳ ፍ/ቤት በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል
- የጽሕፈት መሳሪያዎች፣
- የፅዳት ዕቃዎች፣
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣
- የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችንና
- የሠራተኛ ደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ::
በዚሁ መሰረት : –
- ተጫራች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ሰነዱን ከወረዳው ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ ::
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የዕቃው አይነት ህጋዊ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ በስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መለያ ቁጥር(Tin No) ያላቸው እና የገ/ኢ/ትብብር ሚኒስቴር ባዘጋጃቸዉ ዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ከጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተመሰከረ በCPO የጨረታ ዋስትና ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
- አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈርሙ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ካሸነፈባቸው ጠቅላላ ዋጋ 10% ብር በCPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታው ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገው ኤንቨሎፕ በማድረግ በጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20/02/2013 ዓ/ም ከሰዓት በኋላ በ8:00 ሰዓት አደኣ በርጋ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል::
- ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ላሽነፋበት የዕቃው ዓይነት ውል በሚፈርምበት ወቅት የእያንዳንዱን የዕቃ ዓይነት ሳምፕል (sample) በዓይነት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያሽነፋትን ዕቃዎች ከራሳቸው ወጪ እስከ አደኣ በርጋ ወረዳ ፍ/ቤት ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡ እንጭኒ ወረዳ ፍ/ቤት
ስልክ፡0112860010/0910615933
በምዕራብ ሸዋ ዞን የአደአ በርጋ ወረዳ ፍ/ቤት