የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በባሌ ዞን የመዳ ወላቡ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ 2013 ዓ.ም’ በሴፍትኔት ካፒታል ባጀት ለሚሰሩ ፕሮጀክት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በቢዲሬ ቀበሌ አካባቢ ለሚሰራዉ ፒቲሲ (PTC) ስራ ግንባታ
የጨረታ መስፈርቶች / በመዘኛዎች/
- GC/BC7 እና ከዚያ በላይ ::
- የ2012 ዓመት የግንባታ ስራ ፍቃዱን ያሳደሰ እና የ2012 የስራ ፍቃድ ያሳደሰ
- የ2012ዓ/ም የስራ ግብር አጠናቆ የከፈለ ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር INያለወና የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
- ከቆርቆሮ እና ስሚንቶ ውጪ ተፈላጊ የግንባታ ስራ ቁሳቁሶችን ሁሉ የሚያቀርብ በቂ የሰው ሃይል ያለውና ከዚህ በፊት ለሰራቸው ስራዎች ሁሉ ማስረጃ ያለውና ማቅረብ የሚችል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው የስራ ቀናት መዲ-ወላቡ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ኮንትራክተሮች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን 1.5% በባንክ በተመከረ CPO ሲያሲይዙ አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ /IMX/ ከደረጃቸው አካል ላይ በቀጥታ ለዚህ ውድድር በዋስትና የተጻፈ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ጨረታው የሚታሸገውና የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ስዓት በወረዳ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር1 የሚከፈት ይሆናል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተወዳዳሪዎች የማይመለስ ኦረጂናልና ፎቶ ኮፒ የጨረታ ሰነድ ዶክመንት/ በሰም በታሸገ ኤምቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ያልታሸገ የጨረታ ሰነድ ፎቶ ኮፒ ማስረጃ በእጅ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- 1ማንኘውም የሚቀርበው ሰነድ ስርዝና ድልዝ የሌለው መሆን አለበት
- የ2012 ፕሮጀክት 100%ያጠናቀቀ እና 2013 በስምምነቱ ሊፈፀም የሚችል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የቸረታ ሰነድ ላይ ፊርማ እና ማህተም ሙሉ መረጃ መኖር አለበት፡፡
- ማንኘውም ተጫራቾች ኦርጅናል ዶክመንት እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በእጅ ይዞ መቅረብ አለበት
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር -0913223248 ወይም 0913623297 መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ማሳሰቢያ፡- በተጨማሪ የፕሮጀክት ዕቃዎች ቆርቆሮ እና ሲሚንቶ በመ/ቤቱ በኩል የሚቀርብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በባሌ ዞን
የመዳ ወላቡ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት