ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2013
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በቡኖ በደሌ ዞን የሚገኝ የድዴሣ ወረዳ ገ/ኢ/ት፡ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኘው የወረዳው መንገዶች ባለሥልጣን ጽ/ ቤት በተለያዩ ቀበሌም የሚገኙትን መንገዶች ሕጋዊ የሆኑትን ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ D8R ወይም D9R ዶዘር በመከራየት የመሬት ሥራ (Erth worK) ማሰራት ይፈልጋል ።
ስለዚህ ተጫራቶች
- ተጫራች ተወዳዳሪዎች ኩባንያ ማሸን በማከራየት የሥራ ፍቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ ።
- ተጫራች ተወዳዳሪዎች በጨረታው ለመወዳደር የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ፤ ማስረጃ ከሀገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት ማቅረብ አለባቸው። እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ 15% ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተፈላጊ የማሽን ዓይክ ከላይ የተገለጹት ሆኖ ከ2010 ወዲህ የተሠሩ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራችች ተወዳዳሪ/ ድርጅት የሥራ ልምድ ያለውን ኦፕሬተር ማቅረብ የሚችልና ኦፕሬተሩ ችግር ከፈጠረ መቀየር የሚችል መሆን አለበት ።
- ተጫራች በሥራ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮች ካሉ ማሽኑ የዶዘሩ/ ጥገና ወጪ በራሳቸው ለመሸፈን ዝግጁ የሆኑ።
- መ/ቤቱ ለማሠራት ካወዳደረው መንገዶች ውስጥ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የማሰራት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተወዳዳሪ አሸናፊ ለሥራው የሚስፈልጉትን ሁሉ ነዳጅ፡ ዘይት፡ ግራሶና ፡ ሌሎችንም ወጪዎች ራሳቸው ለመሸፈን ፈቃደኛ የሆኑ።
- ተጫራቾች ዶዘሩን ጭነው ማቅረብና ከሳይት ሳይት፡ በራሳቸው ወጪማጓጓዝ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታውን ተወዳድረው ካሸነፉ 10 ቀናት ውስጥ ዶዘሩን ወደ ሥራ ቦታ ለማስገባት ዝግጁ የሆኑ።
- ተጫራቾች ካሁን በፊት ሥራላይ ከላይ በተዘረዘ ማሽኖች ተወዳድረው አሸንፈው ከሠበት መ/ቤት፤ ከአንድ ዓመት ወዲህ የተሰጣቸው የሥራ ጥራት የምስክር ወረቀት ደብዳቤ ቢያንስ ከሁለት መ/ቤት ማቅረብ አለባቸው
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ብር 20,000( ሃያ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ፡ ሲፕኦ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሠነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት ለመፈረም ዘግጁ መሆን አለባቸው ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ማሽን በቂ ፐርፎርማንስ /ያለው/ ሊኖረው የሚገባ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ የውል ስምምነት ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 20% ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ በሁለት ኮፒ በማድረግ በሰም በማሸግ የሚመለከተውን የድርጅቱን ኃላፊ በማስፈረምና ሕጋዊ ማህተም ኣድርገውበት፡ ማቅረብ አለባቸው። ሆኖም የጨረታ ሣጥን ከተዘጋ በኋላ የማቅረበ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 (አሥራ አምስት) የሥራ ቀናት የጨረታውን ሠነድ ከድዴግ ወረዳ ገቢዎች ባለሥልጣን ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ15ኛው የሥራ ቀን 19/2/2013 ዓም በ6፡00 ሠዓት የጨረታ ሣጥን ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡ 15ኛው ቀን በሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይሠዓት ላይ ይከፈታል።
- መ /ቤቱ የተሻለ ማራጭ ካገኘ ጨረታን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 047 443 023/ 09 41 29 4990 ሁሌም በሥራ ሠዓት መደወል ይቻላል።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በቡኖ በደሌ ዞን
የድዴሳ ወረዳ ገ/ኢ/ት ጽ/ቤት