የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 003/2013
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ አርሲ ዞን የዶዶላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 የበጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉትን
- አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችን
- የጽዳት ዕቃዎችን
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
- የኤሌከትሮኒከ መሳሪያዎች
- የመኪና ጎማዎች
- የሰራተኞች የደንብ ልብሶችና
- ሞተር ሳይክሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ።
- ተወዳዳሪዎች የዘመኑን የመንግሥት ግብር ማጠናቀቃቸውን የሚገልጽ ማስረጃና ንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ መሆን አለባቸው።
- ተወዳዳሪዎች በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉና እንዲሁም የተ/ኣታ (ቫት) ተጠቃሚ መሆናቸውን የማስረጃቸውን ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15(አስራ አምስት የሥራቀናት ሊወዳደሩበት የሚችሉትን ዕቃዎች ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ) ከዶዶላ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ወይም በ22/12/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ፖስታው ታሽጎ በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ ሆኖ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓትተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዶዶላ ከተማ ገንዘብና ኢኮ/ትብብር ጽ/ ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ውስጥ ይከፈታል። ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም። ዕለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ሰነድአንድኦርጅናል እናሁለትየማሸንፎቶ ኮፒ በማድረግ በአንድ እናት ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች/ተወዳዳሪዎች/ ተወዳድረው አሸናፊ በሆኑበት ዕቃዎች እስከ መ/ቤቱ ድረስ በራሳቸው ማጓጓዣ ማድረስ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት አስፈላጊ የሆኑት ማስረጃዎችና ከላይ የተጠቀሱትን ዝርዝር ነገሮችን አሟልተው ሲገኙ ብቻ ይሆናል።
- ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው በ5 ቀን ውስጥ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ ከተራ ቁጥር 1፣2፣3፣4፣5፣6፣እና 7 ለተጠቀሱት ለእያንዳንዳቸው ብር 5000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ላይ የገዙበትን ደረሰኝ ማያያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ባቀረቡት ሰነድ ላይ አድራሻቸውን፣ ስማቸውን፣ ስልክ ቁጥርና ፊርማ ማስፈር አለባቸው።
- ተጫራቾች ውል በሚፈርሙበትጊዜ አጠቃላይ ካሸነፉት ዕቃላይ 10 ፐርሰንት የጨረታ ማስከበሪያ በጽ/ቤቱ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- በዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ የቀረቡት የእቃዎች ብዛት 25 ፐርሰንት ከፍና ዝቅ ሊል ይችላል።
- ተጫራቾች ያስገቡትን ማስረጃና ሰነድ የኔ አይደለምማለትአይችሉም።
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት ተጫርተው ያሸነፉትን ዕቃ ያላቀረቡ መወዳደር አይችሉም፡፡
- ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡት ማንኛውንም ዕቃ ጥራታቸው በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ የተረጋገጠ መሆን አለባቸው።
- ተወዳዳሪዎች በገዙት ሰነድ ላይ ያለ ምንምስርዝ ድልዝ በተዘጋጀ ቦታ ላይ መሙላትና ማህተም ማድረግ አለባቸው።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃ አጠናቀው ገቢ ሲያደርጉ ብቻ ክፍያ ይፈጽማሉ።
- መ/ቤቱ ናሙና እንዲቀርብባቸው ከሰነድ ጋር ተያይዞ የቀረቡትን ዕቃዎች የማምጣት ግዴታ አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች 09-30-92-39-08/09 0631-34-34 ደውሎ ማረጋገጥ ይቻላል።
ዶዶላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት