የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በበረከ ዲስትሪከት በ 2012 የተመረተ ምርት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ፡-
በፊንፊኔ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በበረክ ዲስትሪክት በ2012 የተመረተ የተለያዩ የባህርዛፍ ግንዲላ፣ ወራጅ እና ማገዶ ምርት ውጤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም:-
- የእንጨት፣ የግንዲላ፣ የአጠናና የሌሎች ተዛማጅነት ያላቸው የታደሰ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመከፈል ከቅ/ፅ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 7 ወስደው በጨረታው ላይ መሣተፍ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና፤ የሚከፈትበትና የሚዘጋበት ትከክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለፃል፡፡
- ተጫራቶች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ማስከበረያ ዋስትና 5% /አምስት በመቶ/ በማስላት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሌላው ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0116476110 መደወል ይችላሉ፡፡
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት